Apr 18, 2008

እናንተ ዓይጋዎች፤ ተጃጅላችሁ ባታጃጅሉን ምናለበት!?

በአንድ በኩል ታማኝ ተቃዋሚ ነን ዬምንንሻው ስትሉ ይሰማል፣ ዞር ብላችሁ ደግሞ እነዚህ ታማኝ ተቃዋሚዎች ግን መንግስትን ከማሞገስ ባለፈ ሲቃወሙ ወይም ሲኮንኑ ከተገኙ ግን ፀረ-መንግስት እንደሆኑ አድርጋችሁ ትወነጅሏቸዋላችሁ። እንዳው ነገረ ስራቹህ ሁሉ ግራ ቅጡ የጠፈበት ነው። በርግጥ እውነታው ምን እንድሆን ሳትረዱት ቀርታችሁ ሳይሆን አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ እንድዲሉ ስለሆነ ብቻ ነው።

ይህም ሳያንሳችሁ ተቃዋሚዎቹ ምንም የተሻላ አማራጭ የሌላቸው አክራሪዎችና ብቃት የሌላቸው እያላችሁ ስታወግዙ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎች ይህንን ብቃታቸውን እንዳያጎለብቱ የማትፈፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለምሳሌ ፓርቲያቹህ (ወያኔ) ከኢትዮጵይያ ሕዝብ በዘረፈው ሀብትና ንብረት በልጽጎ ራሱን የቻለ የፓርቲ ሕንጻ ለማሰራት ሢንቀሳቀስ፣ ፓርላማቹህ ደግም ተቃዋሚዎች የገንዘብ ምንጫቸው እንዲያስታውቁ የሚል ሕግ አውጥቷል። በርግጥ ይህ ሕግ ተፈጻሚነቱ ሕግና ዴሞክራሲ በሰፈነበት አገር ቢሆን አግባብነት በኖረው። ሆኖም ግን ራሱ ገዢ ፓርቲው ለህግ ተገዢ ባልሆነበትና ምንም ዐይንነት ዓርዓያነት ባላሳይበት ሁኔታ የሕጉ ቅንነት አጠራጣሪ ነው።

በቅርቡ ደግሙ ከ4 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ይኖርባታል ተብላ በምትገመተው አዲስ አበባ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዴጋፊዎቻቹኅ በሥርቆት የተገኘን ድል ለማክበር ስለተገንኙላችሁ ብቻ ከተማዋ የወያኔ ሆነች ማለታችሁ በጣም አስቂኝ ነው። አባይን ያላየ ምን ያመሠግናል ነው የሚባለው እንኳን!? እስኪ ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ በ1997 በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን አስትታውሱ።

ቢቻል መጀመሪያ ራሳቹህን ሳታሳምኑ ሌላውን ሌላውን ለማሳመን አትሞክሩ!

No comments: